አቶ ታገሰ ጫፎ በኮፕ28 የፓርላማ ምክር ቤቶች የምክክር መድረክ ላይ ተሳተፉ

7 Mons Ago
አቶ ታገሰ ጫፎ በኮፕ28 የፓርላማ ምክር ቤቶች የምክክር መድረክ ላይ ተሳተፉ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ከ28ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP28) ጎን ለጎን በሚካሄደው የፓርላማ ምክር ቤቶች ምክክር ላይ ለመታደም የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ዱባይ ገብተዋል፡፡

አፈጉባኤው የፓርላማ ምክር ቤቶች የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ስለሚኖራቸው ሚና በሚደረገው ምክክር ላይ መካፈላቸው ተጠቅሷል።

አፈጉባኤው በቆይታቸው ከተለያዩ አገራት ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (Pavilion) እንደሚጎበኙም ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መንግስት በተዘጋጀ የእራት ግብዣ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደተደረጋላቸው በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top