ዓለማችን በዕለቱ

7 Mons Ago
ዓለማችን በዕለቱ
 
አፍሪካ
የናይጄሪያ አየር ሀይል የሀገሪቱን የፕሬዚዳንት አውሮፕላን ለሽያጭ አቀረበ።ፋልከን 900 ቢ የተሰኘው እና ፕሬዚዳንቶች ሲገለገሉበት የቆየው አውሮፕላን ሽያጭ በቲውተር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ሽያጩ በሀገሪቱ ፌድራል መንግስት ፀድቋል ነው የተባለው።
አውሮፓ
የኔዘርላንድ መንግስት በ2024 ለዩክሬን 2.7 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገባ።ከ21 ወር በላይ ያስቆጠረው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ኪዬቭን እያዳከማት ነው የሚል ስጋት በምዕራባውያን አጋሮቿ ዘንድ እየጨመረ ነው። የኔዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንክ ብሩዊንስ በዩክሬን ጉብኝት ወቅት እገዛውን ይፋ አድርገዋል።
አሜሪካ
ዋሽንግተን የአውሮፓ አጋሮቿ ለዩክሬን ከኔቶ አባልነት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ቃል ኪዳን እንዳይገቡ ማስጠንቀቋ ተሰማ። ይህን ያሉት አንድ የዩክሬን በቴሌግራም ቻናላቸው ባጋሩት መረጃ ነው። እንደ ባልስልጣኑ ገለፃ ይህ ማስጠንቀቂያ በቀጥታ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አንቶኒ ብሊንከን የተላለፈ ነው።
እስያ
በጋዛ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ እንዳሉት የእስራኤል የቦምብ ጥቃት በደቡብ ፍልስጤም ካን ዩኒስ እና ራፋህ ከተሞች ዙሪያ እየጠነከረ መጥቷል። በጋዛ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ የሆኑት ሪቻርድ ፔፐርኮርን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁኔታው በየሰዓቱ እየተባባሰ ነው። አክለውም ጋዛ የደረሰው ሰብአዊ እርዳታ በጣም ትንሽ ነው፤ የእርዳታ ፈላጊው ቁጥር እና ያለው እርዳታ አይመጣጠንም ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top