ከ21 ወር በላይ ያስቆጠረው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ኪዬቭን እያዳከማት ነው የሚል ስጋት በምዕራባውያን አጋሮቿ ዘንድ እየጨመረ ነው። ይህን ተክትሎም የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
የኔዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንክ ብሩዊንስ በዩክሬን ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የገንዘብ እገዛውን ይፋ አድርገዋል።
ሚንስትሯ ከዩክሬን አቻቸው ዲሚትሮ ኩሌባ ጋር ከተገናኙ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዩክሬን ጎን ነን፤ የእናንተ ደህንነት የእኛ ደህንነት ነው ብለዋል።
ሚንስትሯ ሀገራቸው በሩማንያ ለF-16 ጄቶች የስልጠና ማዕከል እንደከፈተች እና ከአሜሪካ፣ዴንማርክ እና ሌሎች ሀገራትም ጋር በመሆን ዩክሬን ተዋጊ ጄቶቹን በተቻለ ፍጥነት ማሰማራት እንደትችል እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል።
አክለውም ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያላት ፍላጎት በቅርቡ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።