ማሊ እና ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን የግብር ትብብር ስምምነት ሻሩ

1 Yr Ago 402
ማሊ እና ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን የግብር ትብብር ስምምነት ሻሩ

ማሊ እና ኒጀር በግብር ጉዳዮች ላይ ለትብብር እና አስተዳደራዊ እርዳታ ከፈረንሳይ ጋር የገቧቸውን ሁለት ስምምነቶች መሻራቸውን በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ሁለቱ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን በተቆጣጠሩት ወታደራዊ ጁንታዎች የሚተዳደሩ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በፀጥታ እና በሌሎችም ዘርፎች የቅርብ አጋር ከነበረችው የቀድሞዋ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የመገደብ እርምጃ ሲወስዱ ቆይተዋል።

መግለጫው እ.ኤ.አ. በ 1972 ከፈረንሣይ ጋር የተደረገውን ስምምነት የሻረ ሲሆን ይህም ድርብ ግብርን ለማስቀረት እና በተለያዩ የታክስ ጉዳዮች ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ያለመ ነው ተብሏል።

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ድረ-ገጾች ባሰራጨው የጋራ መግለጫ ፈረንሳይ በአገሮቻችን ላይ የምታሳየውን የጥላቻ አመለካከት በእነዚህ ስምምነቶች ኢ ፍትሀዊነት መመልከት ይቻላል ብሏል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top