በጋዛ ያለው ሁኔታ በየሰዓቱ እየከፋ እየሄደ ነው - የዓለም ጤና ድርጅት

2 Mons Ago
በጋዛ ያለው ሁኔታ በየሰዓቱ እየከፋ እየሄደ ነው - የዓለም ጤና ድርጅት

በጋዛ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ እንዳሉት የእስራኤል የቦምብ ጥቃት በደቡብ ፍልስጤም ካን ዩኒስ እና ራፋህ ከተሞች ዙሪያ እየጠነከረ መጥቷል።

በጋዛ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ የሆኑት ሪቻርድ ፔፐርኮርን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁኔታው በየሰዓቱ እየተባባሰ ነው።

ፒፔርኮርን አክለውም ጋዛ የደረሰው ሰብአዊ እርዳታ በጣም ትንሽ ነው፤ የእርዳታ ፈላጊው ቁጥር እና ያለው እርዳታ አይመጣጠንም ብለዋል።

ብዙ ሰዎች ከቦምብ ለማምለጥ ወደ ደቡቡ የጋዛ ሰርጥ እንደሚሄዱ ያነሱት ተወካዩ፤ አሁን ላይ የጤና ስርዓቱ ለወረርሽኝ ተጋላጭ እንደሆነም አሳስበዋል።

በሰሜን ጋዛ በከባድ የቦምብ ጥቃት ምክንያት ሊቋረጥ የተቃረበውን የሰብአዊ አቅርቦት ያመላከቱት ተወካዩ በሰሜን የተከሰተውን ተመሳሳይ ሁኔታ በደቡቡም እንዳናይ ያሰጋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top