ኢትዮጵያ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና የመልማት ዕድል ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል:- በተባበሩት ኤምሬትስ ያሉ ባለሀብቶች

7 Mons Ago
ኢትዮጵያ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና የመልማት ዕድል ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል:- በተባበሩት ኤምሬትስ ያሉ ባለሀብቶች
በዱባይ እየተካሄደ ካለው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አመራጮች በተባበሩት አረብ ኢምሬት ላሉ ኢንቨስተሮች እና የኮፕ-28 ተሳታፊ ትልልቅ ኢንቨስትመን ኩባንያ አመራሮችና ባለቤቶች ገለፃ ተደርጓል፡፡
 
ውይይቱ፤ ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የምትሰጠውን ትኩረት አልሚዎች ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ የሚገጥማቸውን መልካም እድሎች እና የገበያ አማራጮች ለማሳየት የተዘጋጀ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታውቋል፡፡
 
በውይይቱ የተሳተፉ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ የአፍሪካ የስበት ማዕከል እንደሆነች እንደሚረዱ ገልፀዋል፡፡
 
ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በማልማት የሰለጠነ የሰው ኃይሉን እና የገበያ አማራጩን መጠቀም እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡
 
በተመስገን ሽፈራው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top