በሺዎች የሚቆጠሩ የአሽባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ለመንግስት እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ

2 Mons Ago
በሺዎች የሚቆጠሩ የአሽባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ለመንግስት እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ
የህግ የበላይነት ለማስከበር እየተወሰደ ያለውን እርምጃ መቋቋም የተሳናቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ሸኔ አባላት ለመንግስት እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገልጿል::
 
የተወሰደባቸውን እርምጃ መቋቋም ተስኗቸው የተማረኩት ታጣቂዎች ለኦቢኤን እንደ ተናገሩት፤ ሸኔ ክፉኛ ተመትቶ በመፍረስ ላይ ይገኛል::
 
በሌላ በኩል፤ የሸኔ ኃይል በውስጡ በተፈጠረው መከፋፈል እርስ በራሱ ወደ መጠፋፋት የተሻገረ በመሆኑ ለመንግስት እጅ ሰጥተናል ማለታቸውም ነው የተጠቆመው::
 
እንደ ኦቢ ኤን ዘገባ፤ እነዚህ የተማረኩትና በሰላም እጃቸውን ለመንግስት የሰጡ የሸኔ ታጣቂዎች "ሸኔ የፍትህ እና የህዝብ ጥቅም ጠላት በመሆኑ እየፈረሰ ነው" ብለዋል::

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top