"ሙስናን ታግሎ ለማሸነፍ ሙስናን የሚጸየፍ ማኅበረሰብ መገንባት ወሳኝ ስራ ነው" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

2 Mons Ago
"ሙስናን ታግሎ ለማሸነፍ ሙስናን የሚጸየፍ ማኅበረሰብ መገንባት ወሳኝ ስራ ነው" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በጋራ እንታገለው” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የጸረ ሙስና ንቅናቄ መርሀ ግብር አካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሀ ግብሩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት "ከፊት ለፊታችን የተጋረጠውን የሙስና  አደጋ ተፋልሞ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተግባር የተለወጠ፣ ለተመሪዎቹ አርዓያ የሚሆን፣ ለገባው ቃል የሚታመንና የሚኖርለት ዓላማና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሚተላለፍ ሌጋሲ የሚሰራ አመራር ያስፈልጋል" ብለዋል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ታግሎ ለማሸነፍ ሙስናን የሚጸየፍ ማኅበረሰብ መገንባት ወሳኝ ስራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ከንቲባዋ አክለውም "ሀብታችንን በእውቀት በማስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም  የሁላችንንም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top