"የዕድገታችን ጠላት የሆነውን ሙስና በጋራ በመታገል ከሙስና የፀዳ ሥርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል" ፦ ዶ/ር አለሙ ስሜ

7 Mons Ago
"የዕድገታችን ጠላት የሆነውን ሙስና በጋራ በመታገል ከሙስና የፀዳ ሥርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል" ፦ ዶ/ር አለሙ ስሜ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር 20ኛው የዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን "ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው ፣ በህብረት እንታገል" በሚል መሪ ቃል አክብረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ፤ ሙስና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ማነቆ በመሆኑ በተቀናጀ መልክ በህብረት በመታገል ከሙስና የፀዳ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል ።

የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው በበኩላቸው፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሀገራትን ፈጣን ዕድገት እየተፈታተነ የሚገኘው ሙስና ለመከላከል ሀገራት በተለያየ ዘዴ በትኩረት እየሠሩ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያም ሙስናን ለመታገል እየሠራች ትገኛለች ብለዋል።

የሙስና ትግል ሥርዓትን ተቋማዊ በማድረግ ሙስና በተግባር ለመታገል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ይገባል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀ የመጣውን ሙስና በጋራ እንከላከል ሲሉም ጥሪ አቅረበዋል ።

በዝግጅቱ የሙስና አስከፊነትና የትግል ስልት በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በትዕግስቱ ቡቼ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top