በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው

7 Mons Ago
በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው

600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው፡፡

ይህንን እውን ለማድረግ የገንዘብ ሚኒስቴር ከአሜአ ፓወር ኩባንያ ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል፡፡

በሶማሌ ክልል አይሻ አካባቢ የሚገነባው የንፋስ ሀይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት የሚችል ነው ተብሏል፡፡

አጠቃላይ የንፋስ ሀይል ማመንጫው 600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት ሲሆን አሜአ ፓወር በተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ እንደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የ3 አመታት ጥናት ቀድሞ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

ስምምነቱ በመንግስትና በግል አልሚዎች ማእቀፍ የሚሰራ ትልቁ ኢንቨስትመንት ሲሆን በንፋስ ሀይል ማመንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ግዝፉ ይሆናል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በታዳሽ ሀይል ላይ መሰረት ላደረገ የሀይል አቅርቦት ስትራቴጂዋም ስምምነቱ ተጨማሪ ግብአት ይሆናል፡፡

በተመስጌን ሽፈራው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top