የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሮኮ ጭነት ማጓጓዝ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

2 Mons Ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሮኮ ጭነት ማጓጓዝ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ፣ ካዛብላንካ አዲስ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ወደ ሞሮኮ የሚደረገው የጭነት ማጓጓዝ በረራ በሰሜን አፍሪካ መስመር የመጀመሪያው መሆኑንም ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወደ ሞሮኮ የሚደረገው ጭነት ማጓጓዝ በረራ አየር መንገዱ በአፍሪካ ውስጥ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ቁጥር ወደ 34 ከፍ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top