ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ተለዩ

6 Mons Ago
ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ተለዩ

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ሁለት የመጨረሻ እጩዎችን መለየቱን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ አስታወቀ።

እጩ መልማይ ኮሚቴው ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል።

ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ እጩ መልመይ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ መስፈርቶች አምስት ግለሰቦች የተለዩ ሲሆን በመጨረሻም መስፈርቱን ያሟሉ ሁለት እጩዎች መለየታቸው ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ወይዘሮ ሜላተወርቅ ሀይሉ እና አቶ ታደሰ ለማ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው በቦርዱ ተመርጠዋል።

ሁለቱ እጩዎች ባላቸው ልምድና ተሞክሮ የፖለቲካ ገለልተኝነት እና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልተው መገኘታቸው ነው የተገለጸው።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድ ሰብሳቢ የሚያስፈልገው በመሆኑ ሁለቱ እጩዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚቀርቡ ይሆናል።

በመጨረሻም ከሁለቱ አንዱ የቦርዱ ሰብሳቢ እንደሚሆኑና ሹመቱም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

በተስፋዬ ጫኔ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top