አቶ ጥላሁን ከበደ በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ጎበኙ

7 Mons Ago
አቶ ጥላሁን ከበደ በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ጎበኙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የታችኛው የተፋሰሱ አከባቢዎችን ጎብኝተዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ የኦሞ ወንዝ ከመደበኛው የፍሰት መስመሩ በመውጣት ጉዳት ባደረሰበት ዳሰነች ወረዳ በመገኘት ለተጎጂዎች የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።

የኦሞ ወንዝ ሙላት በታችኛው የተፋሰሱ አከባቢዎች እያሰከተ ያለው ጉዳትን  በዘላቂነት ለመከላከል እንደሚሰራ አቶ ጥላሁን ከበደ ገልፀዋል።

የወንዝ ሙላቱ  በየዓመቱ  እያሰከተ ያለው ጉዳትን ለመከላከል ለዘላቂ መፍትሄው ትኩረት በመሰጠት እንደሚሰራም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት።

ችግሩ ከክልሉ መንግስት አቅም በላይ እንዳልሆነ ያስረዱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሰብዓዊ ድጋፍ እና የህክምና አቅርቦትን ጨምሮ ጉዳት በደረሰባቸው አከባቢዎች መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

አደጋው በሰው ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት በመከላከል ረገድ በየደረጃው  የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ብርቱ ጥረት ማድረጋቸውን ተጎጂዎች ገልፀዋል።

ሰብአዊ ድጋፍን ጨምሮ  የመልሶ ማቋቋም ስራ ትኩረት እንዲሰጠውም ጠይቀዋል።

በሚካኤል ገዙ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top