የቡድን 20 አባል ሀገራት ሰፊ እና ወቅታዊ የዕዳ ቅነሳ ዕቅዶችን በመተግበር የተጎዱትን ሀገራት የዕዳ ጫና ለመቀነስ መስራት አለባቸው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

7 Mons Ago
የቡድን 20 አባል ሀገራት ሰፊ እና ወቅታዊ የዕዳ ቅነሳ ዕቅዶችን በመተግበር የተጎዱትን ሀገራት የዕዳ ጫና ለመቀነስ መስራት አለባቸው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፣ዱባይ እየተካሄደ ባለው በ28ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ንግግር አድርገዋል፡፡
 
የቡድን 20 አባል ሀገራት ሰፊ እና ወቅታዊ የዕዳ ቅነሳ ዕቅዶችን በመተግበር፤ የተጎዱትን ሀገራት የዕዳ ጫና ለመቀነስ ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ ፍትሃዊ እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ግባቸውን እንዲያሳኩ መስራት እንዳለባቸው በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ዕዳ ሸክም ከሆነ የትኛውም አገር የአየር ንብረት ፈተናን በብቃት መቋቋም አይችልም ሲሉም ነው የገለጹት።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top