አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሻንዶንግ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ቋሚ ኮሚቴ አባል ከሆኑት ሉዊ ቻንግ ጋር ተወያዩ

7 Mons Ago
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሻንዶንግ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ቋሚ ኮሚቴ አባል ከሆኑት ሉዊ ቻንግ ጋር ተወያዩ
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሻንዶንግ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ቋሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት ሉዊ ቻንግ የተመራ ልዑክ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው መወያየታቸውን ገለጹ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ልዑኩ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ባለው ሁለንተናዊ ግንኙነት እና ርዕሰ መስተዳድሩ በቅርቡ በቻይና፣ ቼንዱ እና ሻንጋይ ከተሞች ያደረጉትን የስራ ጉብኝት ተከትሎ ወደ ሀገር መምጣቱን ነው የገለጹት።
 
በውይይቱ በክልሉ ስላሉ ዕድሎች እና ዕምቅ ሀብቶች ገለፃ ማድረጋቸውን አቶ ሽመልስ ጠቅሰው፤ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማቶች አብሮ ለመሥራትና ያሉትን ልምዶች መጋራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top