ኢትዮጵያ እና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

2 Mons Ago
ኢትዮጵያ እና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
በውይይታቸው፤ አምባሳደር ምስጋኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተከታታይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
 
ግንኙነቱን ለማጎልበት በቀጣይ የሁለትዮሽ አሰራሮችን መፈተሽ እና የፖለቲካ ምክክር ማድረግ እንደሚገባም መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top