እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለተጨማሪ አንድ ቀን አራዘሙ

7 Mons Ago
እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለተጨማሪ አንድ ቀን አራዘሙ
እስራኤል እና ሃማስ ዛሬ ያበቃ የነበረውን የ6 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ አንድ ቀን አራዝመዋል፡፡
 
እስራኤል የተኩስ ስምምነቱ እንዲቀጥል ሃማስ በየቀኑ 10 ታጋቾችን መልቀቅ እንዳለበት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠች ሲሆን ዛሬ የሚለቀቁ ታጋቾች ስም ዝርዝር ባለቀ ሰዓት እንደደረሳት በመግለጽ ነገ በድጋሚ ልትጀምር የነበረውን ውጊያ ለጊዜው እንደተወች ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
 
የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ባወጣው መግለጫ "አደራዳሪዎች ታጋቾችን ለማስለቀቅ እያደረጓቸው ባሉ ጥረቶች እና በተደረሰው የስምምነት ማዕቀፍ መሰረት የውጊያው ኦፕሬሽን በጊዜያዊነት ቆሟል" ብሏል፡፡
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋዛን "በከፍተኛ የሰብዓዊ ውድመት እና ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ቀጣና" ሲሉ የገለጹ ሲሆን እሳቸው እና ሌሎች ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙ በቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲተካ ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
 
በተያያዘ ዜና - ዮርዳኖስ ለጋዛ ድጋፍ የሚያስተባብር እና የተመድ እንዲሁም ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች የተሳተፉበት ስብሰባ በርዕሰ መዲናዋ አማን ዛሬ በዝግ ማካሄዷን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።
 
7 ሳምንታት ባስቆጠረው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ከ14 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን እና ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላውያን መሞታቸው ተገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top