ቱርክ ለአፍሪካ ሀገራት የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

8 Mons Ago
ቱርክ ለአፍሪካ ሀገራት የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

ቱርክ ለአፍሪካ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ እና በቱርክ ሕዝብ እና መንግሥት መካከል ጠንካራ ግንኙት መፈጠሩን ያስታወቁት አምባሳደሩ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር በጋራ ለሚሠሩ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች ለኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማጎልበት ትልቅ መሠረት ናቸው ብለዋል።

“በቱርክ በትምህርት ገበታ ላይ ከሚገኙ 1 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መካከል 690 ተማሪዎች የነፃ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚዎች ናቸው” ብለዋል።

ከ61 ሺህ በላይ አፍሪካዊያውን ተማሪዎች በቱርክ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደሩ፣ ከእዚህም መካከል 15 ሺህ የሚሆኑት በቱርክ መንግሥት ነፃ የትምህርት ዕድል የተሰጣቸው ናቸው ብለዋል።

ቱርክ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር 7 የባህል ማዕከላትን፣ በ26 ሀገራት 191 ትምህርት ቤቶችን (7ቱ በኢትዮጵያ) መገንብቷንም አውስተዋል።

አምባሳደር በርክ ባራን፣ የፊታችን ጥር ወር ይፋ በሚሆነው ነፃ የትምህርት ዕድል ወይም ስኮላርሺፕ ኢትዮጵያውን ተማሪዎችም ተጠቃሚ ለመሆን ፎርም እንዲሞሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ላለፉት አራት ቀናት በዲጂታል ጆርናሊዝም ለኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ያዘጋጀው ሥልጠና ተጠናቅቋል።

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top