በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑት የስኳር ህመምተኞች በሽታው እንዳለባቸው አያውቁም ተባለ

9 Mons Ago 405
በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑት የስኳር ህመምተኞች በሽታው እንዳለባቸው አያውቁም ተባለ

“የስኳር ህመም አጋላጭ ሁኔታዎችን ይገንዘቡ፤ ምላሹንም ይወቁ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የስኳር ህሙማን ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማኅበር በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ነፃ ምርመራ እያደረገ ነው፡፡

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ የስኳር እና የሆርሞኖች ህክምና ስፔሻሊት የሆኑት ዶ/ር ጌታሁን ታረቀኝ እንደገለፁት፤ ህብረተሰቡ በደሙ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እንዲውቅ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

ዘንድሮ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የስኳር ህሙማን ቀን ስለ ስኳር ህመም ለህብረተሰቡ ትምህርት የሚሰጥበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮያ 70 በመቶ የሚሆኑት የስኳር ህመምተኞች የስኳር ህመም እንዳለባቸው እንኳን እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡

እድሜው 35 በላይ የሆነው ሰው በዓመት ቢያንስ አንድ ጊዜ የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ አንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top