ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በናይሮቢ ከፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

10 Mons Ago 459
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በናይሮቢ ከፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ወርቅነህ ለፕሬዚዳንት ሩቶ በቅርቡ በሳውዲ ዓረቢያ ስለተካሄደው የጅዳ የሰላም ሂደት ገለፃ ማድረጋቸውን ከዋና ጸሐፊው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኢጋድ ተባባሪ አመቻችነት በአሜሪካ እና በሳውዲ ዓረቢያ የተጀመረው የጅዳ የሰላም ሂደት ዓላማ በሱዳን 7 ወራት ያስቆጠረውን ግጭት ለማስቆም ነው።

ዶ/ር ወርቅነህ በውይይቱ ወቅት የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዲሁም የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀ መንበር ኢስማኢል ኦመር ጌሌህን ጨምሮ የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እያደረጉት ላለው ጥረት እና ድጋፍ አመስግነዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top