በሞሮኮ የደረሰው ርዕድ መሬት 2.8 ሚሊዮን ሰዎችን መጉዳቱ ተገለፀ

2 Mons Ago
በሞሮኮ የደረሰው ርዕድ መሬት 2.8 ሚሊዮን ሰዎችን መጉዳቱ ተገለፀ

በሞሮኮ የደረሰው ርዕድ መሬት 2.8 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባቸው በድምሩ 2,930 መንደሮች ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ባለፉት ሳምንታት በደረሰው እና በሬክተር ስኬል 6.8 በተመዘገበበት ርዕድ መሬት ከ2,900 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ አብዛኞቹም ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ተራራማ አካባቢዎች ይገኙም እንደነበር ተጠቅሷል።

በአደጋው ቢያንስ 59,674 ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 32 በመቶው ሙሉ በሙሉ መፍረሳቸውን ባለስልጣነቱ ገልፀዋል።

የሀገሪቱ መንግስት በአዳገው ለተጎዱ አባወራዎች በየወሩ 2,500 ድርሃም (244 ዶላር) እርዳታ እንደሚሰጥ፣ በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ቤታቸው ለወደመባቸው ሰዎች 140,000 ድርሃም ካሳ እና በከፊል ቤታቸው ለተጎዳባቸው ደግሞ 80,000 ድርሃም እንደሚከፍል ተገልጿል ።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ1960 ወዲህ በሞሮኮ ታሪክ እጅግ አስከፊ የሆነው ርዕድ መሬቱ በአትላስ ተራሮች ላይ ብቻ ብዙ መንደሮችን ማውደሙ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ ሞሮኮ ከርዕድ መሬቱ በኋላ ለሚካሄደው የመልሶ ግንባታ እቅድ 120 ቢሊየን ድርሃም ወጪ ለማድረግ ያቀደች ሲሆን፤ ይህም በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን መገለፁ የሚታወስ ነው።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top