ዓለማችን በዕለቱ መስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም

10 Mons Ago
ዓለማችን በዕለቱ መስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም

አፍሪካ

የሱዳኑ መሪ በሃገሪቱ ያለውን ጦርነት ለማቆም 'የድርድር መንገድ' እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብድል ፋታህ አል-ቡርሃን በጀነራል ሐምዳን ዳጋሎ ከሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር የሚደረገው ጦርነት ለማቆም 'የድርድር መንገድ' እንደሚደግፉ ገልፀዋል፡፡

በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር ያደረጉት ጀነራል አል ቡርሃን ፓርቲያቸው የሰላም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀው፤ የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሱዳን ከባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለች ሲሆን በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ አገር ጥለው ተሰደዋል።

 

እስያ

ባንግላዲሽ ለፍልስጤም መብት ምንጊዜም ትዋጋለች ሲሉ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።

የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባንግላዲሽ ለፍልስጤማውያን መብት መከበር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እ.ኤ.አ. በ1948 እስራኤል ነፃነቷን ባወጀችበት ወቅት ፍልስጤማውያን እንዲሰደዱ የተገደዱበት የናክባ ከስተት 75ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል።

 

አውሮፓ

የቀድሞ የጣሊያን ፕሬዝዳንት ናፖሊታኖ በ98 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

ኮሚኒስት የነበሩት እና ጣሊያን በ2011 ከእዳ ቀውስ ውስጥ እንድተወጣ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የቀድሞ የጣሊያን ፕሬዝዳንት ጆርጂዮ ናፖሊታኖ በ98 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

 

ደቡብ አሜሪካ

በኮስታሪካ በሰዎች ላይ የሚፈፀም የግድያ መጠን ከመቼውም ጊዜ መጨመሩ ተገለፀ፡፡

በኮስታ ሪካ እስካሁን ከ656 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ይፋዊ የግድያ መረጃ መዝጋቢ ተቋም ጠቅሷል፡፡

ተቋሙ ምንም እንኳን ይህን መረጃ ቢያቀርብም የሃገሪቱ መንግስት በዚህ አመት መጨረሻ ይህ አሃዝ ከ900 በላይ እንደሚያሻቅብ አስታውቋል።

 

አሜሪካ

አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከያ ቢሮ መቋቋሙን አስታወቀች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀገሪቱን የጅምላ ጥቃት ለመቀነስ እንዲያስችል በዋይት ሀውስ የመጀመሪያው የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከያ ቢሮ መቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top