ካናዳ ለዩክሬን 650 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባች

2 Mons Ago
ካናዳ ለዩክሬን 650 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባች

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በኦታዋ ባደረጉት ጉብኝት ለዩክሬን ተጨማሪ 650 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶን በካናዳ ጉብኝታቸው ወቅት ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሶስተኛው የጉብኝት ጉዟቸው ሀገራቸው የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ለምታደርገው ትግል አለም አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

እንደ ቲአርቲ ወርልድ ዘገባ ካናዳ በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ትልቁ የዩክሬን ዲያስፖራ መገኛ ስትሆን እና በጦርነቱ ወቅትም ከፍተኛ ድጋፍ ስታደረግ የቆየች ሀገር መሆኗ ተጠቅሷል፡፡

ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በካናዳ ፓርላማ ተገኝተው፣ በየካቲት ወር 2022 የሩስያ ወታደሮች በዩክሬን ድንበሮች ላይ መታየት ከጀመሩ አንስቶ ካናዳ ለኪዬቭ ስታደርግ ለቆየችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top