አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከያ ቢሮ መቋቋሙን አስታወቀች

1 Yr Ago 281
አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከያ ቢሮ መቋቋሙን አስታወቀች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀገሪቱን የጅምላ ጥቃት ለመቀነስ እንዲያስችል በዋይት ሀውስ የመጀመሪያው የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከያ ቢሮ መቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቢሮው መቋቋሙን አስመልክቶ በዋይት ሀውስ ባሰሙት ንግግር "ከእያንዳንዱ የጅምላ ጥቃት በኋላ፣ በመላው አገሪቱ አንድ ቀላል መልእክት እንሰማለን፤ አንድ ነገር አድርጉ፣ እባካችሁ አንድ ነገር አድርጉ የሚል ድምፅ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁልጊዜ አካላዊ እና ስሜታዊ ጠባሳ የሚተወዉን ይህን አሳዛኝ ክስተት ለመከላከል አስተዳደራቸው ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የጦር መሳሪያ ጥቃትን ለመከላከል ፅ/ቤቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት በአሜሪካ ውስጥ ዜጎች ጠመንጃ እንዲይዙ የሚፈቅዱ ህጎችን ለመዋጋት ቃል እገባለሁ ብለዋል።

ቢሮው በፌደራል ደረጃ መቋቋሙ አዲስ የፖሊሲ ተነሳሽነትን ባያጠቃልልም አስተዳደሩ የመሳሪያ ጥቃትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት የተማከለ፣ የተፋጠነ ያተናክከረ እንዲሆን ያደርገዋል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንተሩ አክለውም፣ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ጉዳዩ ለአስተዳደራቸው እና ለአገሪቱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ግልጽ መልእክት ለመላክ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

አዲስ በተቋቋመው የጦር መሳሪያ ጥቃት መከላከል ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር ሆነው የሚያገለግሉት ስቴፋኒ ፊልድማን "የመሳሪያ ጥቃትን ለመቀነስ ስራችንን የምናፋጥንበት ጊዜ አሁን ነው ፣ ለዚህም ነው ይህንን ቢሮ ያቋቋምነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የ2024 የድጋሚ ምርጫ ዘመቻ የጦር መሳሪያ ጥቃትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሮይተርስ ዘግቧል።

አሜሪካ ባለፉት ዓመታት ከ500 በላይ የመሳሪያ ጅምላ ጥቃት ማስተናገዷን እና በዚህም ከ30,000 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top