የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የጦር ውጊያ ታሪክን ይቀይራል የተባለለት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) የታገዘ "ባራክ" የሚል ስያሜ ያለው ታንክ ይፋ ማደረጉን አስታውቋል፡፡
በወታደራዊ የጦር አቅም ታሪክ "አዲስ ዘመን" እንደሚያመጣ የተነገረለት ይህ ታንክ መሳሪያውን ለሚያንቀሳቀሱ ሰራተኞች የ360 ዲግሪ የጦር ሜዳ ግንዛቤን ይሰጣል ተብሏል፡፡
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት፤ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ ስለሚሰራው እና "መብረቅ" የሚል ትርጓሜ ስላለው ታንክ እንዳሉት "የመሳሪያው መፈጠር የወታደራዊ አቅማችንን ወደ ሌላ ደረጃ የሚያድርስ እና የቴክኖሎጂ አቅማችን በምን ደረጃ እንደሚገኝ የሚሳይ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ታንኩ በቀላሉ በአቅራቢያው ለሚገኝ ሌላ ታንክ መረጃን ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን፤ በዚህም ወዲያውኑ ምላሽ እንደሚሰጥ እና በመረጃው የቀረለበለትን ኢላማ ለይቶ መምታት አንደሚችልም ተጠቅሷል።
የታንኩ ኦፕሬተሮች በመጪው ጊዜያት ከመሳሪያው ጋር ይበልጡኑ የሚተዋወቁባቸውን የተለዩ መተገበሪያዎች ለመጠቀም በታንኩ ላይ የንክኪ ስክሪን መሳሪያዎች መገጠማቸውም ተገልጿል።
ታንኩ ከዚህ በተጨማሪም ተዋጊዎች በቅርብ ርቀት ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችላቸው የላቀ ምልከታ እና በምሽት ውስጥ ያሉ ሁነቶችን በግልፅ ማየት የሚያስችል አቅም እንዳለውም የፎክስ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።