የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጀመሪያዎቹ የዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የደኅንነት አመራር ቻርተር ፈራሚዎች አንዱ ሆነ

2 Mons Ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጀመሪያዎቹ የዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የደኅንነት አመራር ቻርተር ፈራሚዎች አንዱ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጀመሪያዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር /IATA/ የደኅንነት አመራር ቻርተር ፈራሚዎች አንዱ መሆኑን አስታወቀ።

ቻርተሩ የኢንዱስትሪው ሥራ አስፈፃሚዎች በድርጅቶታቸው ውስጥ አዎንታዊ የደኅንነት ባህል እንዲያዳብሩ ለማገዝ ከዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አባላት እና ከሰፊው የአቪዬሽን ማኅበረሰብ ጋር በመመካከር የተዘጋጀ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የደኅንነት አመራር ቻርተር ስምንት ዋና ዋና የደኅንነት አመራር መርሆዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር የድርጅቶቹን የደኅንነት ባህል ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተነግሯል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top