ዓለማችን በዕለቱ - መስረም 11/2016 ዓ.ም

2 Mons Ago
ዓለማችን በዕለቱ - መስረም 11/2016 ዓ.ም
አፍሪካ
 
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሀገሯ በፍጥነት እንዲወጣ ጥያቄ አቀረበች፡፡
 
 
አውሮፓ
 
6 ፖርቹጋላዊያን ወጣቶች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር ሀላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል 32 የአውሮፓ ሀገራትን ፍርድ ቤት ከሰሱ፡፡
 
 
እስያ
 
ሳኡዲ አረቢያ እና እስራኤል ግንኙነታቸውን ለማደስ የጀመሩት እንቅስቃሴ በየቀኑ ይበልጥ እንዲቀራረቡ እያደረጋቸው መሆኑን የሳኡዲው ልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ተናገሩ።
 
 
አሜሪካ
 
ኒው ዮርክ ውስጥ የተማሪዎች ባስ ተገልብጦ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 5 ሰዎች ክፉኛ ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ተነግሯል፡፡ 44 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የተማሪዎች አውቶብስ አደጋ ያጋጠመው የፊት ጎማው ላይ በነበረበት ብልሽት ሳቢያ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top