ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተመድ ሰላም አስከባሪ ከሀገሯ እንዲወጣ ጠየቀች

10 Mons Ago
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተመድ ሰላም አስከባሪ ከሀገሯ እንዲወጣ ጠየቀች
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሀገሯ በፍጥነት እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባለች፡፡
 
በ78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቴሼኬዲ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችን ማስቆም እና ንፁሀን ዜጎችን ከጥቃት መከላከል አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
አክለውም አሁን ጊዜው ሀገሪቱ ግዛቷን ተቆጣጥራ ሰላሟን በራሷ የምታስጠብቅበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እ.ኤ.አ በ2020 የተመድ ሰላም አስከባሪ ከሀገሪቱ እንዲወጣ የውሳኔ ሃሳብ ቢያቀርብም አሜሪካ ባለመስማማቷ ወታደሮቹ መቆየታቸው አል ጃዚራ ዘግቧል፡፡
 
የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚንቀሳቀሱ አማፂያንን ለመከላከል ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የገባው ከ25 አመት በፊት ነበር፡፡
 
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ 15 ሺህ የሚደርሱ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top