በቀዳማዊት እመቤት የተገነባው የረገ ኤያት ትምህርት ቤት ድጋፍ ተደረገለት

1 Yr Ago 126
በቀዳማዊት እመቤት የተገነባው የረገ ኤያት ትምህርት ቤት ድጋፍ ተደረገለት

 

በቀዳማዊት እመቤት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተገነባው የረገ ኤያት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ የብዝሀ ህይወት ኢኒስቲትዩት ድጋፍ ተደረገለት፡፡

 

ኢኒስቲትዩት የቤተመጽሐፍት ቤተ ሙከራ እና የአይሲቲ ዕቃዎችን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ነው ለትምህርት ቤቱ ያስረከበው፡፡

 

የትምህርት ቁሳቁሶቹን በአካል ቦታው ድረስ በመገኘት ለትምህርት ቤቱ ያስረከቡት የኢንስቲትዩቱ ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ ናቸው፡፡

 

ድጋፉ የነገ ተረካቢ ህጻናትን በእውቀት የበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ዶ/ር ፈለቀ ተናግረዋል፡፡

 

በኢኒስቲትዩቱ የተደረገው ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ሥራ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ያሉት ደግሞ የአበሽጌ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ም/ኀላፊ እያሱ ሰሎሞን ናቸው፡፡

 

በዮሐንስ ፍስሃ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top