“X” (ኤክስ) የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር ደንበኞችን ማስከፍል ሊጀምር ነው- ኤሎን ማስክ

1 Yr Ago 208
“X” (ኤክስ) የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር ደንበኞችን ማስከፍል ሊጀምር ነው- ኤሎን ማስክ
የቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ስሙ “X” (ኤክስ) የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር ደንበኞችን ማስከፍል ልጀምር መሆኑን የኩባንያው ባለቤት ኤሎን መስክ ገለጸ፡፡
 
በተለይም ኢንተርኔትን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን በመጠቀም በ“X” የጥላቻ ንግግር የሚያስፋፉ አካላትን ለመቆጣጠር ወርሃዊ መጠነኛ ክፍያ አስፈላጊ መሆኑን ኤሎን መስክ ገልጿል ሲል ታይምስ ዘግቧል፡፡
 
የአከፋፈሉ ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡
 
በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ “X” ገጽ ላይ በየዕለቱ እስከ 200 ሚሊዮን ገደማ የጥላቻ ንግግር ይዘቶች እንደሚጫኑ ተገልጿል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት የኤክስ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከማስታወቂያ የሚገኝ ገንዘብ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top