ጣሊያን ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ገለጹ፡፡
የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዎ ታጃኒ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ እንዲሁም ከኤርትራ እና ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
በኒው ዮርክ እየተካሄደ ባለው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሀገራቱ፣ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በኢንቨስትመንት ፣ ንግድ እንዲሁም በሠላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡