የግሪክ የረድኤት ሠራተኞች በሊቢያ በአደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል

1 Yr Ago 150
የግሪክ የረድኤት ሠራተኞች በሊቢያ በአደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል
በምሥራቃዊ ሊቢያ የምትገኘው ዴርና ከተማ ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ በደረሰው አሰቃቂ የጎርፍ አደጋ የሟቾች አስከሬን አሁንም በቁፋሮ እየተገኘ ነው።
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በሳምንቱ መጨረሻ በዴርና 11 ሺህ 300 ሰዎች መሞታቸውን እና 10 ሺህ100 ሰዎች መጥፋታቸውን መግለጹን ተከትሎ ግራ መጋባት ተፈጥሯል፡፡
 
‘OCHA’ የሟቾችን ቁጥር ያገኘው ከሊቢያ ቀይ ጨረቃ እንደሆነ የገለጸ ሲሆን፣ የቀይ ጨረቃ ቃል አቀባይ ታውፊቅ አል ሹክሪ ግን አሃዙን ውድቅ በማድረግ ይፋዊ ቁጥሮቹ የወጡት በሊቢያ ባለስልጣናት በተፈቀደው ኤጀንሲ በኩል ነው ብሏል።
 
'OCHA' ዘግይቶ ባወጣው ሪፖርት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት አሃዞችን ጠቅሶ 3 ሺህ 958 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች አሁንም መጥፋታቸውን ገልጿል።
የሊቢያ የመረጃ ተንታኞች እና ተመራማሪዎች ቡድን ቅዳሜ ዕለት በተደረገ ቆጠራ ወደ 4 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።
 
የምሥራቃዊ ሊቢያ መንግሥት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ኦትማን አብደል ጃሊል እስካሁን ድረስ 3 ሺህ 283 ሰዎች መሞታቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከፈረንሳይ፣ ኢራን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ቱኒዚያ፣ ቱርክ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በቦታው ደርሰው እየተረባረቡ ነው።
 
ወደ ሊቢያ የተላኩት አምስት የግሪክ የሰብአዊ እርዳታ ቡድን አባላት ደግሞ በትራፊክ አደጋ መሞታቸውን የግሪክ ጦር ሰኞ ዕለት አስታውቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top