ባህር ዳር ከተማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የቱኒዝያውን ክለብ አፍሪካንስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱን የማሸነፊያ ግቦች ሀብታሙ ታደሰ ለጣና ሞገዶቹ አስቆጥሯል።
ባህር ዳር ከተማ የመልስ ጨዋታውን ከሳምንት በኋላ ከሜዳው ውጪ የሚያደርግ ሲሆን በድምር ውጤት የሚያሸንፍ ከሆነ ሀገራችንን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ምድብ ድልድል ውስጥ ይካተታል።