ጀርመን እና ቤልጄም ከጨረር ጋር በተያያዘ የአይፎን ምርትን ሊያግዱ ነው

1 Yr Ago 209
ጀርመን እና ቤልጄም ከጨረር ጋር በተያያዘ የአይፎን ምርትን ሊያግዱ ነው

ጀርመን እና ቤልጄም ከጨረር ጋር በተያያዘ የአፕል ምርት የሆነውን "አይፎን 12" የእጅ ስልክ ሊያግዱ መሆኑን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡ ፈረንሳይ ምርቱን ከሁለት ቀናት በፊት ማገዷ ተገልጿል፡፡

"አይፎን 12" ወደ ሰውነት የሚገባው የጨረር መጠን ከተፈቀደው መጠን በ40 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑ ነው የፈረንሳይ ተመራማሪዎች የገለጹት፡፡

 

ይህን ተከትሎ ጀርመን እና ቤልጄም "አይፎን 12" የተባለውን ተንቀሳቃሽ ስልክ ሊያግዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

ጣሊያን እና ስፔን ደግሞ ሁኔታውን እያጤኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በ"አይፎን 12" ተንቀሳቃሽ ስልክ የቀረበውን ክስ ተከትሎ የአፕል ኩባንያ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

 

ስልኩ ከበርካታ የዓለም አቀፍ የጨረር ተቋማት ዕውቅና አግኝቷል ሲል ኩባንያው ክሱን እንዳልተቀበለው  ተገልጿል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top