ኢትዮ-ቴሌኮም የ5ኛው ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
የ5G የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በሰከንድ እስከ 10 ጊጋባይት የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት እንዳለው ነው የተገለጸው።
አገልግሎቱን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ ይህ አገልግሎት በአዲሱ ዓመት ዋዜማ መጀመሩ አዲስ ተስፋን የሚሰንቅ ነው ብለዋል።
የ5G ኔትወርኩ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መጀመሩም ተገልጿል።