ሩሲያ እና ዩክሬን ከጦር ሜዳ የመራቅ ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም - የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

10 Mons Ago
ሩሲያ እና ዩክሬን ከጦር ሜዳ የመራቅ ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም -  የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በህንድ ኒው ዴልሂ፣  ከሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ሞስኮ እና ኪየቭ መካከል ያለውን ግጭት በቅርቡ ለመፍታት የሚሆን ተስፋ የለም ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናግረዋል።

ጉቴሬዝ በቅርቡ ሰላማዊ መፍትሄ እናገኛለን የሚል ተስፋ የለኝም፤ ሁለቱ ወገኖች አሁንም በግጭቱ ለመቀጠል የወሰኑ ይመስለኛል ሲሉም አክለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የቅርብ ጊዜ አሃዞች እንደሚያመለክቱት፤ በቅርብ ወራት ዩክሬን 66ሺህ ወታደሮች እና 7ሺህ600 ከባድ መሳሪያዎችን በማሠማራት በኬርሶን እና በዶኔትስክ ክልሎች መካከል ያለውን የሩስያን መከላከያ በመልሶ ማጥቃት ለመቁረጥ ሲሞክሩ ተስተውሏል።

መገናኛ ብዙሃን የኪየቭ ምዕራባውያን ደጋፊዎች ይህንን መልሶ ማጥቃት እንደ ውድቀት ቆጥረውታል ብለው መዘገባቸውንም አርቲ ይዞት የወጣው ያመለክታል።

ነገር ግን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ አሁንም ወታደሮቻቸው የቀድሞ የዩክሬን ግዛቶችን ማለትም ኬርሶን፣ ዛፖሮዢያ፣ ዶኔትስክ እና የሉሀንስክን  እንዲሁም ክሬሚያን እንደሚያሰመልሱ እየዛቱ ይገኛሉ።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top