ሩሲያ እና ሳዑዲ አረቢያ ለዓለም ገበያ የሚቀርብ የነዳጅ አቅርቦት ቅነሳን እስከ 2023 መጨረሻ ድረስ አራዘሙ

10 Mons Ago
ሩሲያ እና ሳዑዲ አረቢያ ለዓለም ገበያ የሚቀርብ የነዳጅ አቅርቦት ቅነሳን እስከ 2023 መጨረሻ ድረስ አራዘሙ

ከሐምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው በቀን አንድ ሚሊዮን በርሜል  ነዳጅ የሳዑዲ አረቢያ ቅነሳ ለተጨማሪ ሶስት ወራት እስከ 2023 መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥል የሀገሪቱ ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 

የሩሲያ ነዳጅ የውጭ ንግድ በቀን 300ሺህ በርሜል ቅነሳም በተመሳሳይ ለሶስት ወራት  እንደሚቀጥል የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ባለፈው ጥቅምት ኦፔክ+ በቀን ሁለት ሚሊዮን በርሜል ምርትን ለመቀነስ መስማማቱ ይታወሳል።

ውሳኔው በወቅቱ ዩናይትድ ስቴትስን ያስቆጣ ሲሆን፤ የአሜሪካ አጋር የነበረችው ሳዑዲ አረቢያም በዩክሬን ጦርነት ከሩሲያ ጋር ወግናለች በሚል ቁርሾ ውስጥ መግባታቸው ጋር ተደማምሮ ጉዳዩ ተካሯል። የሳዑዲ ዕለታዊ የነዳጅ ምርት በቀን  ዘጠኝ ሚሊዮን በርሜል የሚደርስ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር ካላት በቀን 12 ሚሊዮን በርሜል  የማምረት አቅም በጣም ያነሰ መሆኑን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top