የሽብር ቡድኑ እየተወሰደበት በሚገኘው ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ በኦሮሚያ ክልል ጉሜል ደሎ እና ሊበን ወረዳ አካባቢዎች የሚገኙ ታጣቂዎቹ እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ እየሰጡ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በተሳሳተ ትርክት ወደ ሽብር ቡድኑ እንደተቀላቀሉ እና በተሳሳተ ዓላማ ለበርካታ ዓመታት የኦሮሚያን ህዝብ ለዘመናት ሲበድሉ መቆየታቸውን የገለፁት ታጣቂዎቹ ለመከላከያ ሰራዊቱ እጃቸውን ከመስጠት ውጪ ሌላ ምንም አመራጭ የለንም ማለታቸው ተገልጿል።
በጫካ ውስጥ የሚገኘው ታጣቂ ሃይል፤ እየተወሰደበት በሚገኘው እርምጃ ተስፋ በመቁረጥ እየተበታተነ እንደሚገኝ እና ምንም የማድረግ አቅም እንደሌለውም ተናግረዋል።
እጃቸውን የሠጡ የቡድኑ አባላት፤ ሌሎችም የወጣትነት እድሜያቸውን በጫካ ውስጥ ከማሳለፍ ይልቅ፤ ለሰራዊቱ እጃቸውን በመስጠት ቀሪ ህይወታቸውን በሰላማዊ መንገድ መምራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።