የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

1 Yr Ago 8647
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተወለዱ በ37 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ከአባታቸው አቶ ክፍሌ ወ/ኢየሱስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘብይደሩ ዱሬሳ በ1978 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ካዛንችስ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትለዋል።

ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ በሥራ ዓለም በክርስቲያን ሎየር ፌሎሽፕ፣ በአይርሽ ኤይድ፣ በወርልድ ቪዥን እና አስከ ኅልፈተ ሕይወታቸው በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

የወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነሐሴ 29 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በጴጥሮስ-ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመልክቷል።

ወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ባለትዳር እና የ2 ሴት ልጆቾ እናት ነበሩ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወ/ሮ ምስጋና ክፍሌ ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል። 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top