የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ዶ/ር ፍትሕ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

10 Mons Ago
የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ዶ/ር ፍትሕ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰረዎች ፌዴሬሽን በሚል ስያሜ የሀገሪቱ የሆቴል እና መሰል አገልግሎት ባለቤቶችን አባል አድርጎ ሲሰራ የነበረው አሁን ስያሜውን የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን በማለት የሰየመው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ትላንት እና ዛሬ ባደረገው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር ፍትሕ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጧዋል። ፌዴሬሽኑ አስራ አንድ የቦድር አባላትን የመረጠ ሲሆን፤

  • ዶ/ር ፍትሕ ወልደሰንበት - ፕሬዝደንት - ከሀዋሳ
  • አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን - ተ/ም/ ፕሬዝደንት - ከባህር ዳር
  • አቶ ቴዎድሮስ ደበላ - ም/ ፕሬዝደንት - ከጅማ
  • አቶ ዘውዱ በላይ - ዋና ጸሀፊ - ከቢሾፍቱ
  • አቶ ዮሐንስ ወልደጊዮርጊሰ - ሂሳብ ሹም - ከላሊበላ
  • አቶ ወርቁ ታምራት - የቦርድ አመራር - ከባህር ዳር
  • አቶ ሳሙኤል ታፈሰ - የቦርድ አመራር - ከአዲስ አበባ
  • አቶ አየነው ሀብቴ - የቦርድ አመራር - ከአርባምንጭ
  • ኢንጂ. መሀመድ አህመድ - የቦርድ አመራር - ከጅማ
  • ወ/ሮ ሂሩት ጸጋዬ - የቦርድ አመራር - ከድሬዳዋ
  • አቶ አለማየሁ ድንቁ  - የቦርድ አመራር - ከሀረር

በፌዴሬሽኑ ሕገ-ደንብ መሰረት ለዘርፉ ባደረጉት አስተዋጽዎ እና በፈጠሩት የሥራ ዕድል የፌዴሬሽኑ የበላይ ጠባቂ እና የክብር አባላትንም ሰይሟል፤

  • ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ - የበላይ ጠባቂ - ከሀይሌ ሆቴሎች
  • አቶ ጀማል አህመድ - የክብር አባል - ከሸራተን ሆቴሎች
  • አቶ ታዲዎስ ጌታቸው - የክብር አባል - ከኩሪፍቱ ሆቴሎች
  • አቶ በላይነህ ክንዴ - የክብር አባል - ከኢትዮጵያ ሆቴሎች
  • ወ/ሮ ጸደይ አስራት - የክብር አባል - ከካልዲስ ካፌ እና ሬስቶራንት
  • አቶ አቶ ትዕዛዙ ኮሬ - ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ማዕከል እና ሆቴሎች
  • አቶ በቀለ ሞላን (በቤተሰቦቻቸው) - የምግዜም የክብር አባል

ያደረገ ሲሆን በትላንት ውሎውም የሀገሪቱ የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ያለውን አቅም፤ ያለበትን ተግዳራቶች እንዲሁም ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች ከሀገር አቀፍ ደረጃ በማስጠናት የቀረብ ሲሆን የፌዴሬሽኑም የቀጣይ አምስት ዓመታት የሚሰራበትን ስትራቴጂክ ፕላን ቀርቦ በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች በአባላቱ እና በባለድርሻ አካላት አስገምግሞ ጉባኤው አጽድቆታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top