በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

9 Mons Ago
በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

ዛሬ ምሽት በተካሄደው የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡

በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺህ ሜትር የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ ርቀቱን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፣ ሰለሞን ባረጋ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

በምድቡ አሜሪካዊው ፊሸር ግራንት 3ኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል፡፡

በውድድሩ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ለሜቻ ግርማ አቋርጦ ወጥቷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top