ዓለማችን በዕለቱ - ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

1 Yr Ago 784
ዓለማችን በዕለቱ - ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

አፍሪካ

የአፍሪካ ሕብረት በሃገሪቱ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባትን ጋቦን ከአባልነት አግዷል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በአንድ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 74 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡  

 

አውሮፓ

በሴት የቀዶ ጥገና ሀኪሞች የታከሙ ሰዎች በሕይወት የመኖር ዕድል በወንድ የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ከታከሙት አንጻር ከፍተኛ መሆኑን በጃማ ሰርጀሪ መጽሄት የሰፈረው ጥናት አመለከተ፡፡

 

ኢስያ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይ ላይገኙ እንደሚችሉ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

 

አሜሪካ

ሰዎች ስልክ ቁጥር ሳይለዋወጡ በድምጽ እና በምስል መደዋወል የሚችሉበትን መንገድ ትዊተር ሊጀምር መሆኑን የመተግበሪያው ባለቤት ኤሎን መስክ አስታወቀ፡፡

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top