በሴት የቀዶ ጥገና ሀኪሞች የታከሙ ሰዎች በሕይወት የመኖር ዕድል በወንድ የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ከታከሙት አንጻር ከፍተኛ መሆኑን በጃማ ሰርጀሪ መጽሄት የሰፈረው ጥናት አመለከተ፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ናሙና በመውሰድ የተሰራው ጥናት፤ ሴት ሀኪሞች በቀዶ ጥገና የተሻለ ውጤት ማስመዝገባቸውን አረጋግጧል፡፡
በቀዶ ጥገና ወቅት ሴቶች ከወንዶች አንጻር ጊዜ ወስደው እና ተረጋግተው ሥራውን ማከናወናቸው የሰው ሕይወት የማትረፍ እድላቸውን ከፍ አድርጎታል ይለል የጥናቱ ውጤት፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያለውን የውሳኔ አሰጣጥ ሁኔታንም ጥናቱ ዳሷል፡፡
ሴት የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በጥንቃቄ በመለየት ረገድ ከወንዶች ተሽለው መገኘታቸውን የጃማ ሰርጀሪ መጽሄት ላይ የሰፈሩ የተለያዩ አገራት ጥናቶች አረጋግጠዋል ፡፡
አዲሱ ግኝት በቀዶ ጥገና ሕክምናው ዘርፍ ሴቶች እና ወንዶችን በማጣመር የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል የሚለውን ተስፋ ፈንጥቋል ሲል የዘገበው ዘ ኢንዲፔንደንት ነው፡፡