ሰዎች ስልክ ቁጥር ሳይለዋወጡ በድምጽ እና በምስል መደዋወል የሚችሉበትን መንገድ ትዊተር ሊጀምር መሆኑን የመተግበሪያው ባለቤት ኤሎን መስክ አስታወቀ፡፡
አዲሱን የትዊተር መደዋወያ መንገድ አንድሮይድንም ሆነ አይኦኤስ የሚጠቁሙ የመገናኛ ቁሳቁሶች ላይ እንደሚሠራ ኤሎን መስክ ገልጿል፡፡
"የኔ አለማ አብዮታዊ በሆነ መንገድ ሰዎች የሚገናኙበትን ሁኔታ መቀየር ነው" ብሏል ቢሊዮነሩ ኤሎን መስክ፡፡
በቅርቡ ትዊተር ተግባራዊ አደርገዋለው ያለው ፕላትፎርም በየትኛው ጫፍ ያሉ የዓለማችን ነዋሪዎች ስልክ ቁጥር ሳይለዋወጡ በድምጽም ሆነ በምስል መገናኘት ያስችላል ተብሏል፡፡
ይህም ትዊተርን ሁሉን አቀፍ መተግበሪያ የማድረግ አካል መሆኑን ኤሎን መስክ በትዊተር ገጹ አጋርቷል፡፡