የቻይናው ፕሬዚዳንት በቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይገኙ ይችላሉ ተባለ

9 Mons Ago
የቻይናው ፕሬዚዳንት በቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይገኙ ይችላሉ ተባለ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይ ላይገኙ እንደሚችሉ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

የቡድን 20 አገራት ስብሰባ ቀጣይ ሣምንት በሕንድ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በስብሰባው ላይ የዓለማችን ሁለቱ ሀያል አገራት መሪዎች ጆ ባይደን እና ሺ ጂንፒንግ ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

መድረኩ በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ያለውን የንግድ እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ ሚናውን እንደሚጫወት የፖለቲካ ተኝታኞች ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

ሆኖም የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በስብሰባው አለመገኘት በሁለቱ ሀያላን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የነበረውን መልካም አጋጣሚ ያሳጣል እየተባለ ይገኛል፡፡

ይሁንና የቻይናው መሪ በቡድን 20 አገራት መገኘት አለመገኘትን በተመለከተ ከቻይና በኩል በይፋ የተነገረ ነገር አለመኖሩን ዘገባው አመልክቷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top