የአፍሪካ ሕብረት ጋቦንን ከአባልነት አገደ

3 Mons Ago
የአፍሪካ ሕብረት ጋቦንን ከአባልነት አገደ

የአፍሪካ ሕብረት በሃገሪቱ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባትን ጋቦን ከአባልነት አግዷል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሠላም እና ደህንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ በሃገሪቱ የነበረው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በቦታው እስኪመለስ ድረስ ጋቦን ከአባልነት ታግዳ እንደምትቆይ  አስታውቋል፡፡

ሕብረቱ በጋቦን የተደካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ክፉኛ ማውገዙን የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ ያስረዳል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት በያዝነው የፈረጆቹ ወር መጀመሪያ በኒጀር የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ሃገሪቱን ከህብረቱ ማገዱ ይታወሳል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top