በውሃ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡-አምባሳደር ዶክተር ስለሺ በቀለ

11 Mons Ago
በውሃ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል፡-አምባሳደር ዶክተር ስለሺ በቀለ

አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ያለውን የውሃና ኢነርጂ አውደ ርዕይ ዛሬ ጎብኝተዋል።

አውደ ርዕዩ ደመናን በማበልጸግ እንዴት ዝናብ ማግኘት እንደሚቻልና ለተለያዩ ጠቀሜታዎች እንደሚውል፤ በተቃራኒው መሬት በአግባቡ ካልተጠበቀ በዝናቡ ምክንያት የሚደርሰውን የመሬት መሸርሸርና ተያያዥ ችግሮች የሚገልጹ ሁኔታዎች የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም የውሃ ሀብት ለመጠጥ ብቻ ሳይሆን ለምግብ ማምረትም በስፋት እንደሚጠቅም እና ለሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፖወር እንዴት እንደሚውል የተለያዩ ግድቦችን የሚያስጎበኝ ነው ብለዋል።

በግሉ ዘርፍም በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እያመረቱ መሆኑን ለማየት መቻላቸውን ገልጸዋል።

የዚህ አይነቱ አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ተግባራትን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ ሁሉም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

በአውደ ርዕዩ የቀረቡት ስራዎች ከአሁን በፊት በዚህ ልክ ተሰርተው አያውቁም ያሉት አምባሳደሩ ፤ አዳዲስ ስራዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ ዓመታዊ ኤግዚቢሽን ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር እያስተሳሰሩ ማቅረብ ቢቻል መልካም ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top