በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በአንድ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 74 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡
በአደጋው ከሞቱት መካከል ህፃናት እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን፤ ከሃምሳ በላይ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ዛሬ ማለዳ የተከሰተው አደጋ በከተማዋ መሀል የሚገኝ ባለ 5 ፎቅ ህንጻን ያወደመ ሲሆን ፤ የአደጋው መንስኤ በግልፅ አለመታወቁም ተነግሯል፡፡
አደጋው በደረሰበት ህንፃ ላይ በርካታ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ይኖሩ እንደነበር ነው የተገለጸው።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አደጋው የተከሰተበትን ቦታ ከጎበኙ በኃላ ክስተቱ "በከተማው ውስጥ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እንድንጀምር የማንቂያ ደወል ነው" ብለዋል፡፡
መንግስት የአደጋውን መንስኤ እንደሚያጣራም መግለጻቸውን የዘገበው ዘ ኒዮርክ ታይምስ ነው፡፡