በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የገንዘብ ሽልማት ተበረከተ

3 Mons Ago
በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የገንዘብ ሽልማት ተበረከተ
በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻም ፒዮና ለተሳተፉና የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ60 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
 
የብር ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡
 
በተጨማሪም የነሃስ ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ30 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷል።
 
አትሌት ፀሐይ ገመቹ እና ያለም ዘርፍ የኃላው በሴቶች የማራቶን ውድድር ባሳዩት የቡድን ስራ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
በሻምፒዮናው ዲፕሎማ ላመጡ ፣ለተሳተፉ አትሌቶች እና ለአሰልጣኞችም ተለያየ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
ሽልማት የተበረከተላቸው አትሌቶቹ፤ ከ10 ወራት በኃላ በፓሪስ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር የኢትጵያን ህዝብ ለመካስ አስፈላጊውን ዝግጅት እንደሚያደርጉ በመርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡
 
በሽልማት ስነስርዓቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
 
በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2 ወርቅ፣ 4 ብር እና 3 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ማግኘቷ ይታወቃል።
 
ኢትዮጵያ በውድድሩ ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።
 
በላሉ ኢታላ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top