ዓለማችን በዕለቱ ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም

11 Mons Ago
ዓለማችን በዕለቱ ነሐሴ 25/2015 ዓ.ም

አፍሪካ

በወታደራዊ አመራሮች መፈንቅለ መንግስት ተፈጽሞባቸው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የጋቦኑ ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከመኖሪያ ቤታቸው ቀርጸው ባስተላለፉት አጭር የቪዲዮ መልዕክት አለም አቀፉ ማህበረሰብ መፈንቅለ መንግስቱን በመቃወም ድምጹን እንዲያሰማ ጠይቀዋል፡፡

አውሮፓ

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮችና ደህንነት ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል በአፍሪካ እየተፈጸሙ ያሉ የመንግስት ግልበጣዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

እስያ

የህንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ከ10 ቀናት በኋላ ለምታስተናግደው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ዝንጀሮዎችን ከመሰብሰቢያ አዳራሾች የማራቅ ዘመቻ ጀምራለች፡፡ በኒው ደልሂ ከ20 ሺህ በላይ ዝንጀሮዎች መኖራቸው እና በአመት ከ1 ሺ ያለነሰ ሰው እንደሚነክሱም ተዘግቧል፡፡

አሜሪካ

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን እየሸጠች ነው በሚል አሜሪካ ሀገሪቱን ማስጠንቀቋ ተሰምቷል፡፡ ፒዮንጊያንግ ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን በመሸጥ ላይ መሆኗ የተነገረው በአሜሪካ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ጫፍ በደረሰበት ወቅት ነው፡፡  


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top